የኪነ ጥበብ ዘርፍ አገልግሎቶች

1. ለቴአትር አፍቃርያን የተለያዩ የኪነ-ጥበብውጤቶችን በማዘጋጀት ለአገልግሎት ማቅረብ/መስጠት፤ እንዲሁም ሀገራችን የተያያዘችውን የልማትና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ቀጣይነት እንዲኖረው ኪነ-ጥበብንበመጠቀም የንቅናቄ ስራ መስራት ፡፡
2. የሴቶችንና፣ ወጣቶችን ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የኪነጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፡፡
3. ህጻናትን የሚገነቡና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችሉ፤የኪነጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ፡፡
4. የኪነ-ጥበብ ተቋማት ማበልፀግና ማስፋፋት ላይ ጥናት ማሄድ፣
5. የሲኒማ፣ የቴአትር ቤቶች፣ የፊልም ስቱዲዮ መንደር የመሳሰሉት ስራ የሲኒማ-ጥበብ ተቋማትን የማበልጸግ ስራ መስራት፣
6. የግል የሥነ-ጥበብ ኢንተርተይመንት እንዲቋቋሙ ድጋፍ ማድረግ፣ 16. በስነ-ጥበብ ዘርፍ ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠና መስጠት፣
7. ለሀገር በቀል ስነ-ጥበብ ስራዎች ሙያዊ ድጋፍ መስጠትና ማማከር፣
8. የሲኒማና ቴአትር ቤቶችን አሰራር መከታተልና መደገፍና ማበልፀግ፣
9. ሀይማታዊና ሀገር በቀል የስነ-ጥበብ መገልገያ መሳሪያዎችና እውቀት እንዲጠበቁና እንዲተዋወቁ ማድረግ፣
10. በስነ-ጥበብ ዘርፍ የህግ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፣
11. የስነ-ጥበብ ክበባትን አደረጃጀት ደንብ ማዘጋጀት፣
12. የሙያ ብቃት ሰርተፊኬት አዘጋጅቶ መስጠት፣
13. በስነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋማት የቁጥጥር፣ ክትትልና ድጋፍ ስራዎች
14. የምሽት ክበባት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች መስራት፣