አመሠራረት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ግንቦት ወር 2000 ዓ.ም.የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት ለማቋቋም በተዘጋጀው አዋጅ መሰረት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በሚል ስያሜ የተቋቋመ ነዉ፡፡
በዚህም የባህል ዘርፉ ከባህልና ማስታወቂያ ቢሮ የቱሪዝም ዘርፉ ደግሞ ከንግድና እንዱስትሪ ቢሮ ተለይተዉ በአንድ ላይ 17 የሰዉ ኃይል ይዞ እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡
በ2011 ዓ.ም ደግሞ በሀገራችን እና በከተማችን የተካሄደዉን ለዉጥ መነሻ በማድረግ የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ትኩረት ተሰቶት እራሱን ችሎ እንደ ዘርፍ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ በዚህም የቢሮዉ ስያሜ ወደ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ተቀይሯል፡፡
- የባህል ዘርፍ ልማታዊ አስተዋጽኦ እንዲስፋፋ ያድርጋል፤ ባህል፣ ኪነጥበብ፣ ሥነ ጥበብ እና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ግብረ-ገባዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን የሚያራምዱና የሚያስፋፉ እንቅስቃሴዎችን ይከታተላል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፤
- የኪነጥበብ ዘርፉ ...
- የቱሪዝም ዘርፉ...