የባህል ዘርፍ
1. የባህል አገልግሎቶች የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት ፣ ማደስ ፣ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት መዘርጋት፣
2. የባህል እሴቶችን የማሳደግ፣ የማስተዋወቅና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣ መጤ ባህሎችን የመከላከል አገልግሎት፣(መስጠት)
3. ከባህል ዕደ-ጥበቦች አንጻር አገራችን ከዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንድታገኝና በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችም ገቢ እንዲያገኙ፤ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ስልጠና የማመቻቸትና የማስተዋወቅ ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች መስጠት፣
4. በከተማችን የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ማጥናት፣ ማልማት፣ እንክብካቤና እድሳት እንዲያገኙ ማድረግ፤እንዲሁም የምዝገባ ስርአት መዘርጋት ፡፡
5. ከተንቀሳቃሽ ቅርሶችና ከሙዚየም ጋር በተያያዘ ለታሪክ አጥኚዎችና ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት፡፡
6. ለተማሪዎች ብሎም ለከተማዋ ነዋሪዎች፣ የቤተ መጽሐፍት የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት መስጠት አገልግሎቱንም በማዘመን በአይ.ሲ.ቲ የታገዘ ማድረግ/አገልግሎት መስጠት፡፡
7. ለከፍተኛ አመራሮችና በተለያየ እርከን ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የልዩ ቤተመጽሀፍት አገልግሎት መስጠት፡፡ይኸውም የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት፤በሌላ መልኩም ከአመራሩ ጋር አብሮ የሚሄድ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡