በባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የሚሰጡ የሴክተር ዋና ዋና አገልግሎቶች፣
1. የባህል አገልግሎቶች የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት ፣ ማደስ ፣ቁጥጥርና ክትትል ስርዓት መዘርጋት፣
2. የባህል እሴቶችን የማሳደግ፣ የማስተዋወቅና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣ መጤ ባህሎችን የመከላከል አገልግሎት፣(መስጠት)
3. ከባህል ዕደ-ጥበቦች አንጻር አገራችን ከዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንድታገኝና በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችም ገቢ እንዲያገኙ፤ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ስልጠና የማመቻቸትና የማስተዋወቅ ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች መስጠት፣
4. በከተማችን የሚገኙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ማጥናት፣ ማልማት፣ እንክብካቤና እድሳት እንዲያገኙ ማድረግ፤እንዲሁም የምዝገባ ስርአት መዘርጋት ፡፡
5. አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር የቱሪስት መስህቦችን ማልማትና ማስተዋወቅ፣ የቱሪስት መረጃ ስርአት መዘርጋት እንዲሁም በከተማው ውስጥ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ፤ብሎም ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ማረጋገጥ፡፡
6. ለቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙያ ብቃት(ማረጋገጥ/ጫ) መስጠት፣ ማደስ፣ በአገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ የቁጥጥርና ክትትል ስርአት በመዘርጋት የአገልግሎቱ ጥራትና ተደራሽነት፣ ህጋዊነትን ማረጋገጥ፡፡...
7. ከተንቀሳቃሽ ቅርሶችና ከሙዚየም ጋር በተያያዘ ለታሪክ አጥኚዎችና ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት፡፡
8. ለተማሪዎች ብሎም ለከተማዋ ነዋሪዎች፣ የቤተ መጽሐፍት የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት መስጠት አገልግሎቱንም በማዘመን በአይ.ሲ.ቲ የታገዘ ማድረግ/አገልግሎት መስጠት፡፡
9. ለከፍተኛ አመራሮችና በተለያየ እርከን ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች የልዩ ቤተመጽሀፍት አገልግሎት መስጠት፡፡ይኸውም የንባብ ፣ የውሰትና የሪፈረንስ አገልግሎት፤በሌላ መልኩም ከአመራሩ ጋር አብሮ የሚሄድ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
10. ለቴአትር አፍቃርያን የተለያዩ የኪነ-ጥበብውጤቶችን በማዘጋጀት ለአገልግሎት ማቅረብ/መስጠት፤ እንዲሁም ሀገራችን የተያያዘችውን የልማትና የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ቀጣይነት እንዲኖረው ኪነ-ጥበብንበመጠቀም የንቅናቄ ስራ መስራት ፡፡
11. የሴቶችንና፣ ወጣቶችን ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የኪነጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፡፡
12. ህጻናትን የሚገነቡና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችሉ፤የኪነጥበብ ውጤቶችን በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ተደራሽ ማድረግ፡፡
13. የኪነ-ጥበብ ተቋማት ማበልፀግና ማስፋፋት ላይ ጥናት ማሄድ፣
14. የሲኒማ፣ የቴአትር ቤቶች፣ የፊልም ስቱዲዮ መንደር የመሳሰሉት ስራ የሲኒማ-ጥበብ ተቋማትን የማበልጸግ ስራ መስራት፣
15. የግል የሥነ-ጥበብ ኢንተርተይመንት እንዲቋቋሙ ድጋፍ ማድረግ፣
16. በስነ-ጥበብ ዘርፍ ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠና መስጠት፣
17. ለሀገር በቀል ስነ-ጥበብ ስራዎች ሙያዊ ድጋፍ መስጠትና ማማከር፣
18. የሲኒማና ቴአትር ቤቶችን አሰራር መከታተልና መደገፍና ማበልፀግ፣
19. ሀይማታዊና ሀገር በቀል የስነ-ጥበብ መገልገያ መሳሪያዎችና እውቀት እንዲጠበቁና እንዲተዋወቁ ማድረግ፣
20. በስነ-ጥበብ ዘርፍ የህግ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፣
21. የስነ-ጥበብ ክበባትን አደረጃጀት ደንብ ማዘጋጀት፣
22. የሙያ ብቃት ሰርተፊኬት አዘጋጅቶ መስጠት፣
23. በስነ-ጥበብ ማሰልጠኛ ተቋማት የቁጥጥር፣ ክትትልና ድጋፍ ስራዎች
24. የምሽት ክበባት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች መስራት፣