የራስ ቲያትርን በአዲስ መልክ በአዲስ ቦታ ለመገንባት የመሠረተ ደንጋይ የማኖር ስነስርዓት ተካሄደ

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 1081


የራስ ቲያትርን በአዲስ መልክ በአዲስ  ቦታ  ለመገንባት የመሠረተ ደንጋይ የማኖር ስነስርዓት ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በተገኙበት የመሠረት ድንጋዩን የማስቀመጥ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።
ከንቲባ አዳነች አበቤ ጥበብ ሀገር እንደምትገነባና ትውልድ እንደምታነፅ ገልፀው ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሆነውን የራስ ቲያትር በአዲስ መልክ ገንብቶ ለኪነጥበቡ ማህበረሰብ ለማቅረብ መሠረተ ደንጋይ ማኖር ብቻ ሳይሆን ጀመሮ መጨረስን የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በከተማዋ ካሉት ቲያትር ቤቶች ለየት ያለ ዲዛይን ያለው ቲያትር ቤት ለመገንባት በቢሮው የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል አዲስ የቲያትር ቤት ዲዛይንን በባለሙያዎች በማስጠናት እና ንድፉን በማካተት ግንባታው እንዲካሄድ እንደሚደረግ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ተናገረዋል።
ከንቲባዋ እንደዚህ ዓይነት ፕሮጀክቶችን ለትውልድ ሠርቶ ለማስተላለፍ ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ ለሰላም በጋራ እንቁም ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዳሉት ቲያትር ቤቱ ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያን የመገንባት ተልዕኮውን አሁንም ዘመኑን በሚመጠን መንገድ በማስቀጠል ሀገርን የማፈረስ አጀንዳ ያላቸውን ሀይሎች ሴራ ለማከሸፍ በጥበብ እውነትን በመገለጥ ለሀገር ሰላም እና አንድነት የሚገባውን ኃላፊነት እንዲወጡ የኪነጥበብ ማህበረሰቡን ጠይቀዋል።
ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃላፊነት ተረከቦ ግንባታውን እንደሚያስፈፅም የቢሮ ኃላፊዋ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማሪያም ገልፀዋል።

Search
Popular Posts


Leave a Comment: