ለረጅም ጊዜ ተጓቶ የነበረው የወጣቶችና ህፃናት ቲያትር ግንባታ የከተማ አስተዳደር በአንድ አመት ውስጥ ባደረገው ርብብር ወደ መጠናቀቁ ደርሷል፡፡ የሃገር ፍቅር እድሳትም በተመሳሳይ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል !!

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 202


ለረጅም ጊዜ ተጓቶ የነበረው የወጣቶችና ህፃናት ቲያትር ግንባታ የከተማ አስተዳደር በአንድ  አመት ውስጥ ባደረገው ርብብር ወደ መጠናቀቁ  ደርሷል፡፡ የሃገር ፍቅር እድሳትም በተመሳሳይ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል !!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙውን የአዲስ አበባ ሕጻናትና ወጣቶች ቲያትርና የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትን የዕድሳት ሥራ ጥቅል አፈጻጸምን ገመገሙ፡፡
ከንቲባ አዳነች ሁለቱም የቲያትር ቤት ፕሮጀክቶች ከትውልድ የስብዕና ግንባታ አስፈላጊነታቸው አኳያ በተያዘላቸው በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ና ተግዳሮቶችን ለመፍታት ብሎም ለታለመላቸው የትውልድ ግንባታ መዋል እስኪችሉ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል ።
ለትውልድ ግንባታ ትኩረት ሰጥተን በሁሉም ረገድ ከተንቀሳቀሰን አገሩን አብዝቶ የሚወድ ዜጋ መፍጠር እንችላለን ያሉት ከንቲባ አዳነች በሁሉም ረገድ ለተተኪው ትውልድ የሞራልና የስብዕና ግንባታ የሚጠቅሙ ሥራዎችን እየሰራን አጠቃላይ ለውጡን ዕውን እናደርጋለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።
አስቀድመን የትውልድ የስብዕና ግንባታ ላይ በሚገባው መልኩ ባለመሥራታችን ዛሬ እየገጠሙን ያሉ ጭካኔን የተሞላ ተግባራት በወገኑ ላይ ሲፈፀም እያየን በመሆኑ የትውልድ ግንባታ ላይ አበክረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል ከንቲባ አዳነች።
ከዚህም ባሻገር የጥበብ ተቋማት አስተዋጽኦቸው የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች በመላው አዲስ አበባ የጥበብ ስራዎችን በመደገፍ እንዲቻለን ከለውጡ ማግስት አንስቶ አስር አንፊ ቲያትር ቤቶችን የገነባን ሲሆን ጥረታችንን ለወደፊቱም አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል ::

Search
Popular Posts


Leave a Comment: