የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝሞ ቢሮ ከፌድራል ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ታጋይ የሆኑት ኒልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ የሰለጠኑበት የኮልፌ ፖሊስ ማስልጠኛ ተቋምን ከደቡብ አፍሪካ ከኒልሰን ማንዴላ ዩኒቨርስቲ የመጡ የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ወደ ከተማችን ለመጡ ሉሁካን ቡድን ማሰልጠኛውን የማስጎብኘት ስራ ተሰርቷል፡፡
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 2775

የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝሞ ቢሮ ከፌድራል ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ታጋይ የሆኑት ኒልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ የሰለጠኑበት የኮልፌ ፖሊስ ማስልጠኛ ተቋምን ከደቡብ አፍሪካ ከኒልሰን ማንዴላ ዩኒቨርስቲ የመጡ የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ወደ ከተማችን ለመጡ ሉሁካን ቡድን ማሰልጠኛውን የማስጎብኘት ስራ ተሰርቷል፡፡
ልሁካኑን በመቀበል አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ኮሚሽነር ጀኔራል መስፍን አበበ እና የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ደስታ ሎሬንሶ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ በማርሽ ባንድ የደመቀ አቀባበል ተደርጓል፡፡
ልሁካን ቡድኑን በመወከል በደቡብ አፍሪካ የማንዴላ ዮኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ሲቦንጌል ሙታዋና ማቲካ ሁርሶላ የሳውዝ አፍሪካ ምክትል ዲፕሎማት ሚሽን ንግግር ያደረጉ ሲሆን በጋራ ይህን የጥቁር ህዝቦች ታሪካዊ ቦታ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በንግግራቸው ቢሮ ከዮኒቨርስቲው ጋር በቱሪዝም ዘርፍ በጋራ መስራት እንደሚፈልግ የገለፁትን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት እና የኢንባሲው ተወካይ በደስታ እንደሚቀበሉትና በዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
Search
Popular Posts
- የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝሞ ቢሮ ከፌድራል ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ታጋይ የሆኑት ኒልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ የሰለጠኑበት የኮልፌ ፖሊስ ማስልጠኛ ተቋምን ከደቡብ አፍሪካ ከኒልሰን ማንዴላ ዩኒቨርስቲ የመጡ የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ወደ ከተማችን ለመጡ ሉሁካን ቡድን ማሰልጠኛውን የማስጎብኘት ስራ ተሰርቷል፡፡
- በስነ -ጥበባት ህብራዊ መልክ የተዋበች ኢትዮጵያ! በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 2-7 በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትና በጊዩን ሆቴል በተካሄደው 13ኛዉን ከተማ አቀፍ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ማጠቃለያን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሲንፖዚየምና ዝክረ ጥበባት የእውቅና መድረክ በአዝማን ሆቴል ተካሄደ።
- የራስ ቲያትርን በአዲስ መልክ በአዲስ ቦታ ለመገንባት የመሠረተ ደንጋይ የማኖር ስነስርዓት ተካሄደ
- ለረጅም ጊዜ ተጓቶ የነበረው የወጣቶችና ህፃናት ቲያትር ግንባታ የከተማ አስተዳደር በአንድ አመት ውስጥ ባደረገው ርብብር ወደ መጠናቀቁ ደርሷል፡፡ የሃገር ፍቅር እድሳትም በተመሳሳይ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል !!